በፍርድ ቤት እርዳታ ለማግኘት ብዙ መንገዶች አሉ። Legal Aid NSW ተረኛ ጠበቆችን በመላው NSW ወደሚገኙ ሁሉም የአካባቢ ፍርድ ቤቶች እና ሌሎች በርካታ ፍርድ ቤቶች እና ልዩ ፍርድ ቤቶች ይልካል። ተረኛ ጠበቆች የራሳቸው ጠበቃ የሌላቸው ነገር ግን በዚያ ቀን በፍርድ ቤት ክስ ያላቸውን ሰዎች ይረዳሉ።
ተረኛ ጠበቆች ለ Legal Aid NSW የሚሰሩ ወይም እርስዎን ለመርዳት በ Legal Aid NSW የሚከፈላቸው የግል ጠበቆች ናቸው። የት እንደሚገኙ ለማወቅ በእኛ በ NSW ፍርድ ቤቶች እና በልዩ ፍርድ ቤቶች የሚሰጥ እርዳታ ድረገጽ ላይ መመልከት ይችላሉ።
ወደ ፍርድ ቤት ከመሄድዎ በፊት ህጋዊ እርዳታ ማግኘት የተሻለ ነው። ለቡድናችን በ LawAccess NSW በ1300 888 529 ይደውሉ ወይም በዌብቻት ላይ ቡድኑን ለማነጋገር ከኛ ጋር ይወያዩ የሚለውን አዝራር ይጫኑ።
በ Bankstown፣ Blacktown፣ Penrith፣ Mount Druitt እና የ Sutherland የአካባቢ ፍርድ ቤቶች የሚሰጥ እርዳታ
ከተረኛ ጠበቃ የህግ እርዳታ ለመጠየቅ ቀላል መንገድ አለ – በቀላሉ የእኛን የመስመር ላይ ቅጽ ይሙሉ። ቅጹ ፈጣን፣ ለአጠቃቀም ቀላል እና በማንኛውም ጊዜ ሊቀርብ የሚችል ነው። አንድ ጊዜ ከገባ በኋላ፣ የ Legal Aid NSW ሰራተኞች አባል መልሶ ይደውልሎታል። የእርስዎን H ቁጥር የማያውቁት ከሆነ፣ ሲጠየቁ H0000 ያስገቡ። ቅጹ ከላይ ለተዘረዘሩት ፍርድ ቤቶች ብቻ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። |
ማንኛውም ሰው ጉዳዩ በፍርድ ቤት በሚታይበት ቀን የተወሰነ እርዳታ ለማግኘት ወደ ተረኛ ጠበቃ መቅረብ ይችላል።
ጉዳይዎ የበለጠ ውስብስብ ከሆነ፣ ተረኛ ጠበቃው በቀጠሮ እንዲተላለፍ በመጠየቅ ሊረዳዎት ይችላል። የህግ ምክር ወይም ውክልና ማግኘት እንዲችሉ ይህ እስከሚቀጥለው ቀን ድረስ ጉዳይዎን የሚያራዝም ይሆናል። በእኛ የህግ ምክር ድረገጽ ላይ የበለጠ ማወቅ ይችላሉ።
ተረኛ ጠበቃው ለእርስዎ ሊያደርግልዎት ስለሚችላቸው ነገሮች ገደቦች አሉ። ተረኛ ጠበቃ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላል።
በቤተሰብ ህግ ጉዳዮች፣ ተረኛ ጠበቆች እንዲሁ አስቸኳይ የቤተሰብ ህግ ችግሮች ሊረዱዎት ይችሉ ይሆናል – ለምሳሌ የቀድሞ ባለቤትዎ ልጅዎን ካልመለሰች/ካልመለሰ ወይም ወደ ውጭ ሃገር ሊወስዳቸው/ልትወስዳቸው እየዛተ/ች ከሆነ።
በወንጀል ጉዳይ ጥፋተኛ አይደለሁም ብለው ከተከራከሩ እና ጉዳይዎ በዚያ ቀን ለችሎት ከተዘረዘረ በፍርድ ቤት ውስጥ እርስዎን መወከል አይችሉም።
ችሎት ምስክሮች ወደ ፍርድ ቤት መጥተው ስለተፈጠረው ነገር ሲናገሩ እና ዳኛው ወይም ዳኛው በሁለቱም ጠበቆች የቀረቡትን ክርክሮች ግምት ውስጥ ሲያስገባ ነው።
በችሎት ላይ እርዳታ ከፈለጉ ወይም አንድ ሰው እንዲናገርልዎት ከፈለጉ፣ ከችሎትዎ ቀን በፊት Legal Aid NSW ውስጥ ካለ ጠበቃ ጋር ወይም የህግ እርዳታን በደንብ ከሚሰራ ጠበቃ ጋር መነጋገር አለብዎት። ስለዚህ ጉዳይ በእኛ የህግ ምክር ድረ ገጽ ላይ የበለጠ ማወቅ ይችላሉ።
በ NSW ውስጥ ባሉ ሁሉም የአካባቢ ፍርድ ቤቶች፣ ፍርድ ቤቱ በዚያ በሚቀመጥበት ጊዜ በሁሉም የቤተሰብ ህግ ፍርድ ቤት ቦታዎች እና በመላው NSW በሚገኙ ሌሎች ብዙ ፍርድ ቤቶች እና ልዩ ፍርድ ቤቶች ውስጥ ተረኛ ጠበቆች አሉን።
በ NSW ፍርድ ቤቶች እና ልዩ ፍርድ ቤቶች የሚሰጥ እርዳታ ድረገጽ ላይ እርዳታ በአካባቢዎ የሚገኝ መሆኑን ማረጋገጥ ይችላሉ።
ተረኛ ጠበቃን ማግኘት እና በእለቱ እርዳታ ማግኘት ነጻ ነው።
እርዳታ ማግኘት ከቀጠሉ ለህግ እርዳታ ብቁ መሆን እና ለጉዳይዎ ወጪ መዋጮ መክፈል ይኖርብዎታል።
መክፈል ያለብዎት መጠን በሚያገኙት ገቢ እና ባለቤት በሆኑበት ነገር ላይ የሚወሰን ነው።
በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ጉዳዮች ላይ ተረኛ ጠበቃው ምክር እየሰጠዎት ከሆነ ብቻ ወይም የመጀመሪያ ጊዜዎ ከሆነ እና በእስር ላይ ከሆኑ ለህጋዊ እርዳታ ብቁ መሆን አያስፈልግዎትም። ተረኛ ጠበቃው እርስዎን በፍርድ ቤት እየወከለዎት ከሆነ በአጠቃላይ ለህጋዊ እርዳታ ብቁ መሆን አለብዎት።
በቤተሰብ ህግ ጉዳዮች ከተረኛ ጠበቃ ወይም በፍርድ ቤት ከማህበራዊ ድጋፍ አገልግሎቶች እርዳታ ለማግኘት ለህጋዊ እርዳታ ብቁ መሆን አያስፈልግዎትም።
ህጋዊ ቃላት አንዳንድ ጊዜ ለመረዳት አስቸጋሪ ናቸው። እንግሊዝኛ የመጀመሪያ ቋንቋዎ ካልሆነ ወይም በአውስትራሊያ ምልክት ቋንቋ ለመነጋገር ከመረጡ፣ በፍርድ ቤት አስተርጓሚ እንዲረዳዎት ይፈልጉ ይሆናል።
ብዙ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ለአስተርጓሚ የሚከፍል ቢሆንም በተቻለ ፍጥነት ለማደራጀት እነሱን ማነጋገር አለብዎት።
ፍርድ ቤቱ አስተርጓሚ እንደሚያስፈልግ ከወሰነ፣ ጉዳዩን ለሌላ ጊዜ በቀጠሮ ማስተላለፍ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።
እኛን ለማነጋገር አስተርጓሚ ወይም ሌላ የግንኙነት እርዳታ ከፈለጉ፣ እባክዎ ያነጋግሩን የሚለው ድረገጻችን ላይ ያሉትን አማራጮች ይመልከቱ።
ወደ ፍርድ ቤት ሲመጡ የሚከተሉትን ማድረግ አለብዎት፦
በፍርድ ቤት ውስጥ ስለ ደህንነትዎ የሚያሳስብዎት ነገሮች ካሉ ስጋቶችዎን ለመወያየት ከፍርድ ቤት ቀንዎ በፊት ፍርድ ቤቱን ማነጋገር አለብዎት፣ ወደ ፍርድ ቤት ህንጻ ውስጥ ሲገቡ ከጥበቃ ጋር ይነጋገሩ ወይም ወደ ፍርድ ቤት ከመሄድዎ በፊት ከእኛ ጋር ለመመካከር ያነጋግሩን በሚለው ድረገጻችን ላይ ያሉትን ዝርዝሮች ይጠቀሙ።
ተረኛ ጠበቃው ፍርድ ቤት በቀረቡበት ቀን ጉዳይዎን ሙሉ በሙሉ መጨረስ አይችል ይሆናል። ጉዳይዎ የበለጠ የተወሳሰበ ከሆነ፣ የህግ ምክር ወይም ውክልና የማግኘት እድል እንዲኖርዎት ተረኛ ጠበቃው ችሎቱ በቀጠሮ እንዲተላለፍ ለመጠየቅ (ጉዳይዎን ለቀጣዩ ቀን እንዲተላለፍ) ሊረዳዎት ይችላል።
ተጨማሪ የህግ እርዳታ ከፈለጉ፣ ከ Legal Aid NSW የመጡ ተረኛ ጠበቆች ጉዳይዎን ለማስኬድ ለጠበቃ ህጋዊ እርዳታ ለማግኘት እንዲያመለክቱ ሊረዱዎት ወይም ሊያግዙዎት ይችላሉ። ለህጋዊ እርዳታ ያመልክቱ የሚለው ድረገጽ ላይ የበለጠ ማንበብ ይችላሉ። እንዲሁም ሊረዱዎት ወደሚችሉ ሌሎች አገልግሎቶች ልንልክዎት እንችላለን።
የአቦሪጂናል እና የቶረስ ስትሬት ደሴት ነዋሪዎች ከLegal Aid NSW ተረኛ ጠበቆች ወይም ከአቦሪጂናል የህግ አገልግሎት (NSW/ACT) ጠበቃዎች በፍርድ ቤት እርዳታ ማግኘት ይችላሉ።
ከ18 አመት በታች ከሆኑ እና በፍርድ ቤት እርዳታ ከፈለጉ፣ ወደ ወጣቶች ነጻ የስልክ መስመር በ 1800 10 18 10 ይደውሉ።
ነጻ የስልክ መስመሩ ከሰኞ እስከ አርብ ከ9am እስከ እኩለ ሌሊት፣ የ24 ሰአት አገልግሎት ከአርብ 9am እስከ እሁድ እኩለ ሌሊት እንዲሁም በህዝብ በአላት ይሰራል።
የሴቶች የቤት ውስጥ ጥቃት የፍርድ ቤት ጥብቅና አገልግሎቶች በመላው NSW ዙሪያ ባሉ ብዙ የአካባቢ ፍርድ ቤቶች የቤት ውስጥ ጥቃት የሚደርስባቸውን ሴቶች እና ህጻናት ያግዛል።
በቤተሰብ ህግ ፍርድ ቤቶች በቤት ውስጥ ጥቃት የተጎዱ ቤተሰቦችን ለመርዳት ከቤተሰብ የጥብቅና እና የድጋፍ አገልግሎቶች የመጡ ለሴቶችም ሆነ ለወንዶች ድጋፍ የሚሰጡ ሰራተኞች ይገኛሉ።
ከልጆች ፍርድ ቤት የእርዳታ መርሃ ግብር የመጡ ወጣት ሰራተኞች በልጆች ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ወጣቶችን ይረዳሉ።
Share with
Facebook
Twitter
LinkedIn