የህግ ምክር

Legal Advice - Amharic (አማርኛ)

አንድ ጠበቃ በልዩ የህግ ችግርዎ ላይ እርዳታ ሲሰጥዎት፣ ይህንን የህግ ምክር ብለን እንጠራዋለን። የህግ ምክር ከህጋዊ መረጃ የተለየ ነው፣ ይህም የበለጠ አጠቃላይ ሊሆን የሚችል ሲሆን ብዙውን ጊዜ የሚሰጠው ስለ ህጉ በሚያውቅ ነገር ግን ጠበቃ ባልሆነ ሰው ነው።

Legal Aid NSW በ NSW ውስጥ የህግ ችግር ላለበት ማንኛውም ሰው በህጋዊ መረጃ እና ሪፈራል አገልግሎታችን፣ LawAccess NSW አማካኝነት ህጋዊ መረጃ ይሰጣል።

ብቁ ለሆኑ ሰዎች በስልክ እና በ NSW ውስጥ ባሉ ብዙ ቦታዎች ነጻ የህግ ምክር እንሰጣለን።

በምክር ክፍለ ጊዜ ምን መጠበቅ እንዳለብዎ

የህግ ምክር ከፍለ ጊዜዎቻችን ነጻ እና በአጠቃላይ 20 ደቂቃ ያህል ይረዝማሉ። አንድ ጠበቃ ስለ ችግርዎ ሲናገሩ ያዳምጥዎታል፣ አንዳንድ ተከታታይ ጥያቄዎችን ይጠይቅዎታል እንዲሁም ቀጥሎ ምን ማድረግ እንዳለብዎት እንዲወስኑ ያግዝዎታል።

ጠበቃ ከሌለዎት በአጫጭር ሰነዶች እርዳታ ሊሰጡዎት ይችላሉ። ረዣዥም ውስብስብ በሆኑ ህጋዊ ሰነዶች ሊረዱዎት አይችሉም።

እንዲሁም ጠበቃዎ በጉዳይዎ እርስዎን መርዳት መቀጠል ይችሉ እንደሆነ ይነግሩዎታል። መቀጠል የሚችሉ ከሆነ፣ ሰራተኞቹ የህግ እርዳታ ለማግኘት ማመልከቻ እንዲሞሉ ይረዱዎታል።

ከምክር ክፍለ ጊዜዎ በኋላ ተጨማሪ እርዳታ ልንሰጥዎ ካልቻልን፣ የበለጠ እርዳታ ለማግኘት የት መሄድ እንደሚችሉ መረጃ ልንሰጥዎ እንችላለን።

ምክር የምንሰጠው ስለምንድን ነው

ጠበቆቻችን ፖሊስን በሚያካትቱ የወንጀል ጉዳዮች፣ ህጻናትን በሚመለከቱ የቤተሰብ ጉዳዮች ወይም የግንኙነት መፍረስ፣ ወይም መሰረታዊ ፍላጎት እንደ መኖሪያ ቤት፣ የገቢ ድጋፍ ወይም የጤና እና የአካል ጉዳት ድጋፎችን ማግኘት በሚቸገሩበት የፍትሃብሄር ጉዳዮች ላይ ሊረዱዎት ይችላሉ።

የህግ ምክር ማግኘት የሚችለው ማን ነው

የህግ ምክር ለሁሉም ሰው አንሰጥም። አላማችን በ NSW ውስጥ ችግር እያጋጠማቸው ላሉ ሰዎች የህግ አገልግሎቶችን መስጠት ሲሆን፣ ይህንንም ለማሳካት ያሉን ግብዐቶች ውስን ናቸው።

ለምክር ክፍለ ጊዜ እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል

ነጻ የህግ ምክር ልንሰጥዎ ወይም ቀጠሮ መያዝ እንደምንችል ለማወቅ የተሻለ የሆነው መንገድ በ LawAccess NSW የሚገኘውን ቡድናችንን ማነጋገር ነው።

በ 1300 888 529 በመደወል ወይም የመስመር ላይ የዌብቻት አገልግሎታቸውን በመጠቀም ሊያገኟቸው ይችላሉ። ከ 9am እስከ 5pm፣ ከሰኞ እስከ አርብ (ከህዝባዊ በአላት በስተቀር) ክፍት ናቸው።